መኖሪያ ቤቶች ልማትና የመንግስት ህንጻዎች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ መኖሪያ ቤቶች ልማትና የመንግስት ህንጻዎች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
Minimize Maximize
 
መኖሪያ ቤቶች ልማትና የመንግስት ህንጻዎች ኮንስትራክሽን
ኤጀንሲ
 
1.መግቢያ
የአምስት ዓመትየዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተመለከቱትን ሃገራዊ አቅጣጫዎችና ግቦች እንዲሁም በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ የድገት ና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የሁለት ዓመት ተኩል የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ቀሪ ሁለት ዓመት ተኩል የተከለሰ ዕቅድን መሰረት በማድረግ ይህ የሀረሪ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
ይህ ዕቅድ ለቢሮው ተጠሪ ተቋማትና የቅርብ ክትትል የሚያደርግባቸው ዋና ዋና ስራዎች ላይ በማተኮር መነሻ ሁኔታዎች፣ የአፈፃፀም አቅጣጫዎችንና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ያካተተ ነው፡፡በቢሮው ስር የተደራጁ መ/ቤቶችም ያህንን መሪ ዕቅድን መሠረት በማድረግ ዝርዝር ዕቅዳቸው ተዘጋጅቷል፡፡ የአፈፃፀም መርሃ ግብርም በመ/ቤቶቹ ዕቅድ ውስጥ ስራዎች በምዕራፍ ተከፋፍለው ከነአፈፃፀም መለኪያዎቻቸው በዝርዝር ተመልክቷል፡፡
ይህ ዕቅድ በቢሮው ዝርዝር ውይይት ተካሄዶበት እንዲደብር ና የጋራ መግባባት የተደረሰበት ሲሆን በዕቅድ ውስጥ የተካተቱት ፕሮግራሞችም ፕሮጀክቶችን፤ የልማት ሥራ ላይ ያተኮሩ ዋና ዋና ግቦችና ተግባራትን የያዙ ናቸው፡፡
የስምምነት ሰነዱ በሶስት ክፍሎች የተደራጀ ነው፡፡በክፍል አንድ የዕቅዱ መነሻ ሁኔታዎች የተገለፀበት ሲሆን በዚህ ርዕስ ስር የዘርፉ የ2006 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ተገመገመ በክፍል ሁለት የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ ፕሮግራም የትኩረት አቅጣጫዎችን የያዘ ሲሆን በእያንዳንዱ ፕሮግራም ስር ፕሮጀክቶችን ዓላማዎችን፤ ግቦችና ዝርዝር ተግባራት ተዘርዝረዋል፡፡ በክፍል ሶስት የዕቅድ አፈፃፀማችንን ለመከታተል የሚያስችል የክትትል ስርዓትን የያዘ ሲሆን በስሩ የበጀት ዓመቱ የበጀት ዕቅድ እና የአመራር የክትትል የግምገማና ግብረ-መልስ ሥርዓትን አካቷል፡፡