የተቀናጀ የመሬት መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የተቀናጀ የመሬት መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
Minimize Maximize

በሐረሪ ክልላዊ መንግስት

ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
የተቀናጀ የመሬት መረጃፕሮጀክትጽ/ቤት
   የፕሮጀክት ጽ/ቤመረጃ (Background Information)
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸው የከተማ ልማት ዘርፍ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎችና ፕሮግራሞች ውጤታማ እንዲሆኑና እንዲሁም የከተማ ልማት ዘርፍ ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ግቦች የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት የመሬት ልማትና ማጀመንት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ግልጽ ነው፡፡ መንግስት አስተማማኝና ቀልጣፋ የመሬት ልማትና ማኔጀመንት ስርአት ለመግንባትና በከተሞች ያለውን የአሰራር ስርአት ግልጽ፣ ፈጣንና ውጤታማ ለማድረግ በዘርፉ ብዙ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የመሬት ልማትና መኔጀመንት ፕሮግራምን በአስተማማኝ ደረጃ ለማሳካት የተቀናጀ የመሬት መረጃ ስርአት ዝርጋታ መንደፍ ወሳኝ በመሆኑ የመሬትና መሬት ነክ መረጃዎች ተደራጅተው የቅብብሎሽና አጠቃቀም ደህንነታቸው ደረጃውን በጠበቀ አግባብ ስለሚሟሉበትና ስለሚደራጁበት ሁኔታ መንግስት የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ በዚህም መሰረት የመሬት ልማትና ማኔጀመንት ፖሊሲ የመረጃ ስርአቱን በካተተ መልኩ ጸድቆ በሁሉም መሬትና መሬት ነክ ተቋማት ወደ ተግባር በመሸጋገር ላይ ይገኛል፡፡ ከፖሊሲው ማዕቅፎች አንዱ እና መሰረታዊ ጉዳይ ከፌደራል እስከ ታችኛው እርከን ድረስ የመሬት ልማትና ማኔጀመንት መረጃ ዝርጋታን የሚመራ ተቋም ማደራጀት ነው፡፡ በዚህም መሰረት የሀረሪ ክልልም በፖሊሲው ላይ የተገለጹ በመሬትና መሬት ነክ መረጃ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማለትም የተቀናጀ የመሬት ስርአት ለመዘርጋትና የመሬት መረጃ አደረጃጀቱንና አስተዳደሩን ዘመናዊ በማድረግ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አስተማማኝ ስርአት ለመዘርጋት የሀረሪ ክልል የተቀናጀ የመሬት መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡
 
Pages: 1  2  3  4  5  6  7  8  9  10  11  

Document Library Document Library
Minimize Maximize

Showing 6 results.