Background Background
Minimize Maximize

  በሐረሪ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን  ቢሮ

የቢሮው መረጃ/back ground information/

የሀረሪ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 104/2004 ንኡስ አንቀጽ 6 መሰረት  በክልሉ የሚካሄዱትን የከተማና የኮንስትራክሽን ኢንዱሰትሪ ልማት ዘርፎችን የመምራት ፤የማስተባበርና የመደገፍ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ቢሮው በአንድ ቢሮ ሃላፊና  በምክትል ቢሮ ሃላፊ የሚመራና   በአዋጁ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት  በዝርዝር የተመላከተ ሲሆን በጥቅሉ መንግስት የሚያወጣቸውን ዘርፉ የሚመራባቸውን ፖሊሲዎች ፤ስትራተጂዎችን ፤ፕሮግራሞችን እና ህጎችን  አፈጻጸማቸውን በተመለከተ በክልሉ እንዲተገበር አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል ፡፡ አገር አቀፍ የልማት ፕሮግራሞችን አፈጻጸም አስመልክቶ በክልሉ የአስተባባሪነትና ተሳታፊነት ያለው ሲሆን ለአጋር መንግስታዊ ተቋማት ፤ለግል ሴክተርና ለሲቪክ ማህበረሰብ የቴክኒክ ድጋፎችን ይሰጣል፡፡

Pages: 1  2