የቢሮው ሐላፊው መልክት የቢሮው ሐላፊው መልክት
Minimize Maximize

 

የተከበሩ አቶ ሙህየዲን አህመድ

በሀረሪ ህዘብ ክልላዊ መንግስት

የከተማ ልማትና ኮንስትክሽን ቢሮ ኃላፊ መልእክት

 

በሲቪል ሰርቪስ ቢሮ አማከልኝነት የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ማቀጣጠያ መድረክ ላይ በከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ ተቋማት ስር ላሉ በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከክልሉ ባለድርሻ አካላት የክልሉ ነዋሪዎች፤የሐይማኖት ተቋማት የወጣቶችና ሴቶች፤ጥቃቅናንና አነስተኛ ማህበራት ባለሀብትና ነጋዴዎች ለቀረቡት አሰተያየትና ጥያቄ መነሻነት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ እንደሚሰራ ገለጸ ፡፡

ከፍተኛ አመራሩ ተቋማዊ ለውጡን በመምራት መልካም አስተዳደርን ለማሻሻል እቅዶችን አውጥቶ ለመፈጸምና ለማስፈጸም መካከለኛ አመራሩና ሠራተኞች በልማትና መልካም አሰተዳደር አገልግሎት አሰጣት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀልጣፋ ተደራሽ እና ፍትሃዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት የመልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንጻር የህዝብ አገልጋይነትን ስሜት በይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል እንዲያስችል ይረዳል፡፡

 በህዝብ አገልጋይነት ዙሪያ መካከለኛ አመራሩ ሆነ ሰራተኛው ግንዛቤው እየተሻሻለ እንዲመጣ በቁርጠኝነት ለውጡን በመምራት እና በማስቀጠል በሰራተኛው ዘንድ በግንባር ቀደምትነት በሚጠበቅበት የሰራ ድርሻ ሁሉ የለውጥ ሰራዊት ግንባታውን እንዲሁም አጠቃላይ የቢሮውን ስራዎችን በጽናት በመያዝ በከፍተኛ የሰራ መነሳሳት ወደ ስራ መግባት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለማከናወን እንዲረዳ የቢሮያችን ተቋማት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት ለሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ከመቼውም በበለጠ ለሚቀረቡ ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥበትንና ቅሬታዎቹም እንዳይደገሙ በመመዝገብና መንስዔቸውን በማጥናት ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኙበትን አሰራር ተግባራዊ እንዲሆን ለማስቻል፣ የተገልጋይ ቅሬታና አቤቱታ ማሰተነገጃ የተዘጋጀና ሰነድ አልባና ህገ-ወጥ ከአካባቢ ልማት ፕላን በህግ አግባብ እየታየ እንደሚሰራ የወጣቱን ስራ አጥነት ከመቀረፍ አንጻር በቅንጅት እንደሚከናወንና የተነዘዛ ካሳ ክፍያ አሰራሮችን በማሰተካከል ልማት ተነሺዎች የተቀላጠፈ ስራን ይከናወናል፡፡