የቢሮው ሐላፊው መልክት የቢሮው ሐላፊው መልክት

 

አቶ መሀመድ ኑረዲን  

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

ኃላፊ መልዕክት

በከተማ ልማት ስራችን የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ትብብር በማጠናከር መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በማስፋፋት እንዲሁም የከተማችንን እሴት ለማጎልበት በሚያስችለው ኢትዮጵያ ሀገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የሚያስችል እጅግ የተለጠጠ የሁለተኛው የዕድገትና ትራንትፎርሜሽን ዕቅድ ተጀምሮ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሃገር ደረጃ የዘርፉን ተልዕኮ ለመወጣት የወሰደውን ኃላፊነት በላቀ ሁኔታ ማሳካት እንደምንችል ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ የከተማውን ህብረተሰብ ወደ ላቀ የልማት እንቅስቃሴ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት የማስፈጸም አቅም ግንባታ እና የሰራዊት ግንባታ በመደገፍ በከተሞች በስፋት ሲሰተዋል የነበረዉን የኪራይ ሰብሰብነት አመለካከት እና ተግባር ከመዝጋት እንዲሁም ልማታዊነትንና መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንጻር ከፍተኛ ሚና ተጫዉቷል፡፡ ሆኖም ግን የከተማ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ በሚተገበርበት ወቅት በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ላይ እንዲሁም ልማትን ከማፋጠን አንጻር በከተሞች በአፈጻጸም ላይ የተሰተዋሉ ክፍተቶችም ነበሩ፡፡ በመሆኑም እነዚህን ዉስንነቶች ለማረም እንዲቻል ወሳኝ የሆኑ ፖሊሲና ሰትራተጂ ተቀርጾ ትኩረት ተሰጥቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ እነዚህን ስራዎች ቅልጥፍና ባለዉ መልኩ ለማከናወንና በቀጣይ በአገራችን ስራ ላይ የሚዉለዉ ፖሊሲና ሰትራተጂ ልማትን የሚያበረታታ፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን የሚደፍን እንዲሁም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በፍትሃዊነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ሆኖ የተዘጋጀ ሰለሆነ ሰለዚህ ከዚህ አኳያ ለመድረኩ ተልዕኮ መሳካት ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጾኦ ማበርከት ይጠበቅብናል፡፡