Web Content Display Web Content Display
Minimize Maximize

 

የሐረሪ ክልል የከተማልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

መግቢያ

 

የሐረሪ ክልል የከተማልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በአዋጅቁጥር 104/2004 ንኡስ አንቀጽመሰረት በክልሉ የሚካሄዱትን የከተማና የኮንስትራክሽን ኢንዱሰትሪ ልማት ዘርፎችን የመምራት፤ የማስተባበርና የመደገፍ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ቢሮው በአዋጁ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር የተመላከተ ሲሆን በጥቅሉ መንግስት የሚያወጣቸውን ዘርፉ የሚመራባቸውን ፖሊሲዎች፤ ስትራተጂዎችን፤ ፕሮግራሞችን እና ህጎችን አፈጻጸማቸውን በተመለከተ በክልሉ እንዲተገበር አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፡፡ አገርአቀፍ የልማት ፕሮግራሞችን አፈጻጸም አስመልክቶ በክልሉ የአስተባባሪነትና ተሳታፊነት ያለው ሲሆን ለአጋር መንግስታዊ ተቋማት፤ ለግልሴክተርና ለሲቪክ ማህበረሰብ የቴክኒክ ድጋፎችን ይሰጣል፡፡

 ቢሮው በአንድ የቢሮ ሃላፊና በምክትል ቢሮ ሃላፊ የሚመራ ሲሆን በአዋጅ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራትን ለመወጣት የሚያስችለውን አደረጃጀት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ እንዲኖረው የመሰረታዊ የስራ ሂደት ጥናት አጠናቆ በተግባር ላይ ውሏል፡፡ የደንበኞችን እርካታ የሚያረጋግጥ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ፤ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎትን ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ማቅረብን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀውን የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድን ለህዝብ ግልጽ ለማድረግ፤ ተገልጋዮች ያሉዋቸውን መብቶች እና አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ይዟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የቢሮውን ተቋማዊ ራዕይ፤ ተልዕኮ፤ እሴቶች እና ዝርዝር ስልጣንና ተግባራትን አካቷል፡፡ 

Pages: 1  2