ዜና ዜና
Minimize Maximize

የሀረሪ ክልል ንግድና ኢንዱስተሪ ፅ/ቤት በምንዛሬዉ ጭማሪ ምክኒያት በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ ጭማሪ የሚያደርጉ አከፋፈዮች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አሳሰበ፡፡

ከሰሞኑን በሚዲያዉ እየተሰማ ያለዉና እንደ ሀገርም አነጋጋሪ የሆነዉ የዉጭ ምንዛሬ መጨመርን ተከትሎ በአብዛኛዉ አከባቢ ላይ በምርትና አገልግሎቶች ላይ ጭማሪ ታይቷል፡፡ በክልላችንም በአንዳንድ ምርቶች ላይ ይኸዉ ጭማሪ የተስተዋለ ሲሆን በተለይም በመሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ እንደ ፓስታ መኮረኒ ስኳር የመሳሰሉት ላይ የታየዉ ጭማሪ ከምንዛሪ ጭማሪዉ ጋር ተያይዘዉ የሚታዩ መሆናቸዉን የገለፁት የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልፈታህ ኢብራሂም ሲሆኑ በአንዳንድ ምርቶች ላይም የታየዉ ከምንዛሬዉ ጭማሪ በፊት የተሸመቱ ና ተከማችተዉ የተቀመጡ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በንግድና ኢንዱትሪ ፅ/ቤት የሚመራ የደምብ አስከባሪ ና የፖሊስ ኮሚኒቲ ጋር በጋራ በመተባበር ቁጥጥር ና ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኙ አክለዉ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የዋጋ ተመን በማዉጣት የዋጋ ስምምነት በመፍጠር የሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡ የክልሉ ነዋሪዎችም አላግባብ ጭማሪ የሚያደርጉ አቅራቢዎችን ለፅ/ቤቱ ጥቆማ በመስጠት የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በመተዉ በህገ-ወጥ መንገድ ና በአቋራጭ ትርፍን ለማካበት በሚሮጡ ህገ-ወጥ ማህበራት ና አከፋፋዮች ሸቀጣሸቀጦችን በማከማቸት በቀጥታ ለህበረተሰቡ ተደራሽ መሆን የነበረበትን አቅርቦት ለነጋዴዎች በመሸጥ እኩይ ተግባራት ላይ ተሰማርተዋል፡፡ በክልላችንም መሰል ተግባራት በአንዳንድ ሸማቾች ማህበራት ላይ የሚስተዋል ሲሆን በአባዲር ወረዳ መስተዳደር ወገሬት ሸማቾች ማህበር እንዱ ነዉ፡፡ ማህበሩ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን ለአከባቢዉ ህብረተሰብ መታደል የነበረበትነ ዘይት ወደ ሌላ ሸቀጣሸቀጥ መደብር በማስረከቡ ምክኒያት የአባዲር ፖሊስ ባደረገዉ ቁጥጥር ተደርሶበት ጉዳዩ እየተጣራ ይገኛል፡፡

Pages: 1  2  3  4  5  6  7